ሞንትጎመሪ ካውንቲ ያለው አላማ አደገኛ እና ሞት የሚያስከትሉ የትራፊክ ግጭቶችን በ 2030 አመት ላይ ለማስቆም ነው። ይህንን ግብ ላይ ለመድረስ፣ ሲራመዱ፣ ብስክሌት ሲነዱ፣ ዊልቼር ስኩተር ሲጠቀሙ ደህንነት የሚሰማዎትን እና የማይሰማዎትን ነገሮች ከርስዎ ለመስማት እነዚህን ጥቂት ጥያቄዎች ይመልሱልን። አስተያየትዎ የካውንቲ መሪዎች የ 10-አመት የራእይ እና ስትራቴጂ ሲያጎለብቱ በመርዳት መንገዶቻችንን ለሁሉም ደህና እንዲሆኑ እና እንደፈለጉ እንዲጓዙ ለማድረግ ይጠቅማል።
ስለ ራእይ ዜሮ የ 10-አመት ስትራቴጂ ለመማር፣ ወደዚህ ድረገጽ ይሂዱ https://www.montgomerycountymd.gov/visionzero/2030plan.html